የአሰልጣኞች አስተያየት | ስሑል ሽረ 0-0 ኢትዮ ኤሌክትሪክ

በጨዋታ ሳምንቱ የማሳረጊያ ዕለት የተካሄደው እና ያለ ጎል ከተጠናቀቀው የስሑል ሽረ እና የኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታን አድርገዋል።

አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ – ኢትዮ ኤሌክትሪክ

“ጨዋታው ከባድ ነበር። ሁሉም ሰው ማድረግ ያለበትን አድርጓል ፤ ከሌላው ቀን አንጻር ኢንቴንሲቲያችን ዛሬ ብዙ ጥሩ አልነበረም። ብዙ የጎል አጋጣሚዎችን አግኝተናል አልተጠቀምንበትም። አጨዋወታችን በራሱ ኢንተንሲቲ አልነበረውም ፀሐዩ ይሁን ምን አላውቅም።”

ረዳት አሰልጣኝ በረከት ገብረመድኅን – ስሑል ሽረ

“ጨዋታው አሪፍ ነበር ፣ ከሽንፈት እንደመመለሳችን ጨዋታው አሪፍ ነበር። የእኛ ልጆች ብዙ ጎልተው የታዩበት ጨዋታ ነበር ግን እስከ አሁን ያልቀረፍነው ጉዳይ አጨራረሳችን ላይ በጣም መሥራት ይኖርብናል በተለይ በመጨረሻዎቹ ደቂቃ ላይ ያገኘነውን ዕድል ባለመጠቀማችን አቻ ለመውጣት ችለናል።”

ሙሉውን ለማድመጥ – Link