የአሰልጣኞች አስተያየት | ሀዲያ ሆሳዕና 2-0 አዳማ ከተማ

“በእርግጠኝነት የምናገረው የክለቡ አመራሮች ውጤቱን አይፈልጉትም!” አሰልጣኝ ግርማ ታደሠ

“ብልጫ እንደ መውሰዳችን ውጤቱ አይገባንም።” አሰልጣኝ አብዲ ቡሊ

ሀዲያ ሆሳዕና ተከታታይ አራተኛ ድል በአዳማ ከተማ ላይ ማስመዝገብ ከቻለበት ጨዋታ መቋጫ በኋላ አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታን አድርገዋል።

አሰልጣኝ አብዲ ቡሊ – አዳማ ከተማ

“ጨዋታው ጥሩ ነው ፤ መዘናጋቶች እና ቀላል ስህተቶች መታረም አልቻሉም። ብልጫ እንደ መውሰዳችን ውጤቱ አይገባንም። ጨዋታ ስለሆነ የግድ መቀበል ግድ ይላል ስህተት ስትሰራ ትቀጣለህ ያ ነው የታየኝ።”

አሰልጣኝ ግርማ ታደሠ – ሀዲያ ሆሳዕና

“ጨዋታው እጅግ በጣም ጥሩ ነበር። እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው የክለቡ አመራሮች ውጤቱን አይፈልጉትም። ብዙ ችግሮች አሉብን ግን መልስ ማግኘት አልቻልንም ትኩረት ያስፈልገናል።”

ሙሉውን የአሰልጣኞች አስተያየት ለማግኘት ይህንን ይጫኑ 👉 LINK