“የጨዋታ ፕሮግራሙ ለመወዳደር ብቻ ሳይሆን ለምንም አይመችም።” አሰልጣኝ በጸሎት ልዑልሰገድ
“በሁለታችንም በኩል ሙከራዎች ስለነበሩ መጥፎ ጨዋታ ነው ማለት አልችልም።” አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ
ብርቱካናማዎቹ እና ሐምራዊ ለባሾቹ ያለ ግብ ከተለያዩበት የ11ኛው ሳምንት የመጀመሪያ መርሐግብር መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር አድርገዋል።
አሰልጣኝ በጸሎት ልዑልሰገድ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
“ጨዋታው ዛሬ በብዙ ነገር የተሻለ ነበር። ብዙ ግልጽ የግብ ዕድሎች ፈጥረናል። የጨዋታ ፕሮግራሙ ለመወዳደር ብቻ ሳይሆን ለምንም አይመችም። ከስኳድ ዴፕዝ እና ከተጫዋቾች ጉዳት አንጻር እየተቸገርን ነው።”
አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ – ድሬዳዋ ከተማ
“ብዙ ጊዜ በ10 ጨዋታ መቀዛቀዞች ይኖራሉ። በሁለታችንም በኩል ሙከራዎች ስለነበሩ መጥፎ ጨዋታ ነው ማለት አልችልም። አዳዲስ ተጫዋቾች ቼክ እያደረግን ነው እና ወደ ሪትሙ እስኪመጡ ድረስ አታንኪንጉ ላይ ትቸገራለህ ፤ ያ ደግሞ ደጋግመው ሲገቡ የሚስተካከል ነው። ባለኝ መረጃ መሠረት መሐመድኑር ናስር በቅርቡ ወደ ሜዳ ይመለሳል።”
ሙሉውን ለማድመጥ –