የአሰልጣኞች አስተያየት | ሀዋሳ ከተማ 0-1 አርባምንጭ ከተማ

የአሸናፊ ተገኝ የመጨረሻ ደቂቃ ግብ ከወሰነችው ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የአርባምንጭ ከተማው አሰልጣኝ በረከት ደሙ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታን አድርጓል።

አሰልጣኝ በረከት ደሙ – አርባምንጭ ከተማ

“ጨዋታው ጥሩ ነበር ፤ በተከታታይ ሁለት ጨዋታዎችን ተሸንፈን ነበር የተሸነፍንባቸው መንገዶችን መለስ ብለን ስንመለከት የመከላከል አደረጃጀታችን ጥሩ አልነበረም እናም እሱን ማስተካከል ትልቁ የቤት ስራችን ነበር።በሁለቱም አጋማሾች በመከላከሉም ሆነ በማጥቃቱ በሚዛናዊነት መጫወት ችለናል።”

*የሀዋሳ ከተማው አሠልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ የድህረ ጨዋታ አስተያየት ለመስጠት ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።