የአሰልጣኞች አስተያየት | ባህር ዳር ከተማ 0-0 ቅዱስ ጊዮርጊስ

“የገጠምነው ጠንካራውን ጊዮርጊስ ነው።” አሰልጣኝ ደግአረግ ይግዛው

“ቀናችን አይደለም ብዬ ልውሰደው።” አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ

የጣና ሞገዶቹ እና ፈረሰኞቹ ነጥብ ከተጋሩበት ጨዋታ በኋላ የሁለቱም ክለብ አሰልጣኞች ለሶከር ኢትዮጵያ የሰጡትን አስተያየት እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል።


አሰልጣኝ ደግአረግ ይግዛው – ባህር ዳር ከተማ

“ጨዋታው እንዳየኸው ጠንካራ ጨዋታ ነበር። ቅዱስ ጊዮርጊስ በማጥቃት እንቅስቃሴ ላይ የሚሳተፉ ጠንካራ ተጫዋቾች አሉት፤ አማካይ ላይም ታታሪ ናቸው። እንደ አጠቃላይ እንደ ቡድን በጥሩ ሁኔታ እየተገነባ ያለው ቡድን ነው። የገጠምነውም ጠንካራውን ጊዮርጊስ ነው፤ መንፈሱ አልተለየውም ማለት ይቻላል።”


አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

“ጨዋታው ከሞላ ጎደል ጥሩ ነው። ነጥብ መጋራታችን ቢያስከፋኝም እንደ ቡድን ግን በጣም ጥሩ ጨዋታ ነበር። በሁለቱም አጋማሾች በተለያየ መንገድ ለመቅረብ ሞክረናል፤ በመጀመርያው አጋማሽ በጣም ብዙ ዕድሎች አምክነናል። አንዳንድ ጨዋታዎች አሉ ቀናችን አይደለም ብዬ ልውሰደው፤ ለማመን የሚከብዱ ኳሶች አምክነናል።”

ሙሉውን ለማድመጥ