የአሰልጣኞች አስተያየት | ሀድያ ሆሳዕና 3-2 ሲዳማ ቡና

ሀድያ ሆሳዕና አምስተኛ ተከታታይ ድሉን ካስመዘገበበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ ሁለቱ አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታን አድርገዋል።
አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው – ሲዳማ ቡና

“በመጀመሪያው አርባ አምስት በተለይ በመጀመሪያዎቹ አስራ አምስት ፣ ሀያ ደቂቃዎች ተቀደምናል ፤ የመስመር ኳሶችን መቆጣጠር ላይ ትንሽ ደካማ ነበርን። ከዚያም ይባስ ብሎ እንደገና በቀይ ተጫዋች አጣን ፤ ከዕረፍት በኋላ ግን ያንን ታክቲካሊ በደንብ አስተካክለናል መገለጫውም ሁለት ዕኩል ሆነናል።”

አሰልጣኝ ግርማ ታደሠ – ሀድያ ሆሳዕና
“ጨዋታው በጣም አሪፍ ነበር ፤ ምንአልባት ሜዳ ላይ ያየሁት ነገር በጣም በተረጋጋ መልኩ ከተጋጣሚያችን አንፃር ተረጋግተን ለመጫወት በደንብ አቅደን ነበር የመጣነው ፤ መሀል ላይ ብልጫ ለመውሰድ አቅደን ነበር የመጣነው መጀመርያ አጋማሽ ላይ ከጠበቅነው በላይ ነው ተጋጣሚያችን ምቹ ሁኔታ ፈጥሮልናል ብዬ አስባለሁ።”