ደደቢት ከ አዳማ ከተማ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ደደቢት 1-0 አዳማ ከተማ
46′ ዳዊት ፍቃዱ
 
– – – – – –
ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በደደቢት አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡

90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 4 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

83′ ሻኪሩ በግንባሩ ገጭቶ የሞከረውን ኳስ ብርሃኑ ይዞበታል፡፡ አዳማ ጫና ፈጥሮ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

ቢጫ ካርድ
78′ ብርሃኑ ፍስሃዬ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ደደቢት
72′ ዳዊት ፍቃዱ ወጥቶ ብሩክ መኮንን ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አዳማ ከተማ
70′ ሚካኤል ጆርጅ ወጥቶ ዮናታን ከበደ ገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
61′ ምኞት ደበበ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

55′ አዳማ ግብ ከተቆጠረበት በኋላ የአቻነት ግብ ለማግኘት የተሻለ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡

ጎልልል!!!! ደደቢት
46′ ከሳሚ ሳኑሚ ጣጣውን የጨረሰ ኳስ የተቀበለው ዳዊት ፍቃዱ ከመረብ አሳርፏል፡፡

ተጀመረ
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡

የእረፍት ሰአት ቅያሪ – አዳማ ከተማ
ጫላ ድሪባ (15) ወጥቶ ሻኪሩ አላዴ (18) ገብቷል፡፡
— —- —– —— ——-

እረፍት
የመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ግብ ተጠናቋል፡፡

45′ መደበኛው 45 ደቂቃ ተጠናቆ 2 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

43′ በተደራራቢ ዝናብ ምክንያት ጉዳት የደረሰበት የአአ ስታድየም ሜዳ ኳስ በአግባቡ ለማንሸራሸር አስቸጋሪ ሆኗል፡፡

ቀይ ካርድ
36′
ስዩም ተስፋዬ በፋሲካ አስፋው ላይ በሰራው ጥፋት በቀጥታ የቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል፡፡

35′ ጨዋታው የተቀዛቀዘ መልክ ይዟል፡፡ የግብ ሙከራዎች እየተስተናገደ አይደለም፡፡

25′ ጨዋታው በመሃል ሜዳ እንቅስቃሴ ያመዘነ ነው፡፡

21′ ጫላ ድሪባ በፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ የሞከረውን ኳስ ብርሃኔ አውጥቶበታል፡፡

19′ ታፈሰ ተስፋዬ የሞከረው ኳስ የግቡን አግዳሚ ገጭቶ ተመልሷል፡፡

5′ ሳምሶን ጥላሁን ከፍፁም ቅጣት ምት ክልል ጠርዝ የመታው ኳስ ለጥቂት ወጥቷል፡፡

1′ ሳሚ ሳኑሚ በግቡ አቅራቢየ ያገኘውን ኳስ ቢሞክርም ምቱ ጥንካሬ የሌለው በመሆኑ ጃኮብ በቀላሉ ይዞታል፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በአዳማ ከተማ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡

የደደቢት አሰላለፍ
1 ብርሃኔ ፍስሃዬ
29 ምኞት ደበበ – 14 አክሊሉ አየነው – 15 ጆን ቱፎር – 2 ተካልኝ ደጀኔ
7 ስዩም ተስፋዬ – 21 ሄኖክ ካሳሁን – 8 ሳምሶን ጥላሁን – 10 ብርሃኑ ቦጋለ
17 ዳዊት ፍቃዱ – 11 ሳሙኤል ሳኑሚ

የአዳማ ከተማ አሰላለፍ
1 ጃኮብ ፔንዛ
6 እሸቱ መና – 20 ሞገስ ታደሰ – 12 ምንተስኖት አበራ– 4 ወንድወሰን ሚልኪያስ
7 ታከለ አለማየሁ – 8 ብሩክ ቃለቦሬ – 19 ፋሲካ አስፋው – 15 ጫላ ድሪባ
9 ሚካኤል ጆርጅ – 14 ታፈሰ ተስፋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *