የአሰልጣኞች አስተያየት | መቻል 0-0 ኢትዮጵያ መድን

ያለ ጎል ከተጠናቀቀው የመቻል እና መድን ጨዋታ ፍፃሜ በኋላ አሰልጣኞች የድህረ ጨዋታ አስተያየታቸውን ለሶከር ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ – መቻል

“እንግዲህ ትንሽ ጨዋታው የታሰረ ነበር ፣ በሁለቱም በኩል ማለት እችላለሁ ታክቲካሊ ጠበቅ ያለ ጨዋታ ነበር። ክፍተት አይታይበትም ስለዚህ ጥንቃቄ የበዛበት ጨዋታ ነበር ማለት እችላለሁ በዚህ ምክንያት።”

አሰልጣኝ ገብረመድኅን ሐይሌ – ኢትዮጵያ መድን

“ጥሩ ነው ፣ በአጠቃላይ መቻል ካለበት ደረጃ አንፃር ካለው ስብስብ አንፃር እኛ ደግሞ ቡድኑን ቻሌንጅ አድርጎ በተለይ ከዕረፍት በኋላ በጥሩ ተቆጣጥረናቸዋል ፣ ከዚህም በላይ ጥሩ ጥሩ አጋጣሚዎች አግኝተን ነበረ ነገር ግን ውሳኔዎች አንዳንድ ጊዜ አስቸጋሪ ናቸው።”