የአሰልጣኞች አስተያየት | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 0-1 ኢትዮጵያ ቡና

“በደጋፊዎቻችን ታጅበን ለመጫወት ጓጉተናል።” አሰልጣኝ ነጻነት ክብሬ

“እግርኳስን ተወዳጅ ያደረገው ያልተጠበቁ ነገሮችን ማስተናገዱ ነው።” አሰልጣኝ በጸሎት ልዑልሰገድ

ቡናማዎቹ በአንተነህ ተፈራ ብቸኛ ግብ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ካሻነፉበት ጨዋታ በኋላ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ተከታዩን ቆይታ አድርገዋል።

አሰልጣኝ ነጻነት ክብሬ – ኢትዮጵያ ቡና

“ጨዋታውን አቅደን እንደመጣነው ነው ያስኬድነው ፤ ከኳስ ዉጪ ጥንቃቄ እና ማን ቱ ማን ማርኪንግ። የድሬዳዋ ቆይታችን በጣም መጥፎ ባይሆንም በምንፈልገው ልክ አይደለም። ውድድሩ አዳማ ወይም አዲስአበባ ከሆነ ተጨማሪ አቅም ይኖረናል እኛም በደጋፊዎቻችን ታጅበን ለመጫወት ጓጉተናል።”

አሰልጣኝ በጸሎት ልዑልሰገድ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

“ትልቅ ተስፋ አድርገን ነበር የመጣነው በድሬዳዋ የመጨረሻ ቆይታችን 3 ነጥብ ይዞ ለመውጣት። የግብ ዕድሎችን በመፍጠሩ በኩል እኛ የተሻልን ነበር ግን የአጨራረስ ችግሮች ነበሩብን። እነሱ በአቋቋም ስህተት ያገኟትን ኳስ አግኝተው አስቆጠሩ። እግርኳስን ተወዳጅ ያደረገው ያልተጠበቁ ነገሮችን ማስተናገዱ ነው። ያለንበት ቦታ አይገባንም ሞራላችንን ነክቶናል።

ሙሉ አስተያየቶችን ለማድመጥ