የዋልያዎቹ ጊዜያዊ ዓለቃ ከወሳኞቹ ጨዋታዎች በፊት ምን አሉ?

የዋልያዎቹ ጊዜያዊ ዓለቃ መሳይ ተፈሪ በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ወሳኝ የመጨረሻ ዙር ማጣርያ ጨዋታዎች ዙርያ ምን አሉ?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) የመጨረሻ ዙር ማጣርያ ከሱዳን ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ወደ ስፍራው ከማቅናቱ አስቀድሞ የብሔራዊ ቡድኑ ጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ከመገናኛ ብዙኀን አባላት ጋር አጭር ቆይታ አድርገዋል ፤ የሰጡትን ማብራሪያም  እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

ስለ ተጫዋቾች ጉዳት

“ከቡድኑ ጋር በተያያዘ ቸርነት ጉግሳ፣ መሐመድኑር ናስር፣ ቢንያም አይተን ፣ ሬድዋን ናስር እና ፍሬዘር ካሳ በጉዳት ምክንያት አብረውን አይገኙም።
እነሱን ይተካሉ ብለን ያሰብናቸውን ተጫዋቾች ተክተናል ፤ አሁን ሜዳም ላይ የምናየው ነገር ጥሩ ነው።”

ስለ አጥቂ ችግር ?

” ‘ዘጠኝ ቁጥር’ ለመጠቀም እየሞከርን ነው ፤ ካሉትም የተሻለ ነገር ይሰራል ብለን የመረጥነውም ስንታየሁ መንግስቱን ነው።”

ስለ አቋም መለክያ ጨዋታ ?

“ከወዳጅነት ጨዋታ ጋር በተገናኘ በተወሰነ መልኩ ጊዜውም አጭር ነበር ፤ ራሳችንን ከማየት አንፃር፣ አሁን እየሰራን ያለው ‘ታክቲክም’ ከማየት አንፃር ከሀዋሳ ተስፋ ቡድን ጋር ጨዋታ አድርገናል።”