ሀዋሳ ከተማዎች አዲስ አምበል ሰይመዋል

ከዋና አሰልጣኙ ጋር የተለያየው ሀዋሳ ከተማ አዲስ አምበል መምረጡን ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ አሳውቋል።

በአስራ አንድ ሳምንታት የሊጉ ጉዞ ካደረጓቸው አስር ጨዋታዎች ሁለት አሸነፈው ፣ በሦስቱ አቻ እንዲሁም በአምስቱ ደግሞ ሽንፈትን ያስተናገዱት እና በቅርቡ ዋና አሰልጣኛቸውን ዘርዓ ሙሉን በማሰናበት በሁለቱ ምክትል አሰልጣኞች በጊዜያዊነት እየተመሩ የኢትዮጵያ ዋንጫ ጨዋታቸውን ለማድረግ እየተዘጋጁ የሚገኙት ሀዋሳዎች አዲስ አምበል መምረጣቸው ታውቋል።

ክለቡን በቀጣዩቹ ጊዜያት በአምበልነት እንዲመሩ በተደረገው ምርጫ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ቡድኑን የተቀላቀለው የመስመር አጥቂው ቢንያም በላይ የቡድኑ ዋና አምበል አድርገው ስለመመረጡ ያረጋገጥን ሲሆን በ2015 የሊጉን ዋንጫ በማሳካት ኮከብ ተጫዋች ተብሎ የተመረጠው ቢንያም ከዚህ ቀደም በተስፋ ቡድን አምበል ከመሆኑ ውጭ ከፍ ባለ ደረጃ አምበል ሆኖ ሲያገለግል ይህ የመጀመሪያው እንደሚሆን ይጠበቃል ፤ በማስከተል የቀድሞ የቡድኑ ዋና አምበል የነበረው በረከት ሳሙኤል ደግሞ ሁለተኛ አምበል ሲደረግ ግርማ በቀለ ሦስተኛ አምበል በመሆን ተመርጠዋል።