የመቻል ስፖርት ክለብ ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የሌጀንዶች የእግርኳስ አሰልጣኞች ስልጠና በነገው ዕለት ይጀመራል።
80ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ከወራት በፊት ያከበረው መቻል ስፖርት ክለብ ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የዲ ላይሰንስ የአሰልጣኞች ስልጠና ማዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል። ከሳምንታት በፊት የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለሚገኙ የግብ ጠባቂዎች አሠልጣኞች ከውጪ ሀገር በመጡ ባለሙያዎች ስልጠና አመቻችቶ የነበረው ክለቡ አሁን ደግሞ የክለቡ የቀድሞ ተጫዋቾች እንዲሁን በአሁኑ ሰዓት በመጫወት ላይ ላሉ ሌጀንዶች የዲ ላይሰንስ ስልጠና አዘጋጅቷል።
በነገው ዕለት ጃን ሜዳ አካባቢ በሚገኘው በክለቡ ጽሕፈት ቤት የሚጀመረው ይህ የካፍ ዲ ላይሰንስ የዲፕሎማ ስልጠና ላይ በአሁኑ ሰዓት በወንዶች ቡድኑ ውስጥ ግልጋሎት እየሰጡ የሚገኙት ሽመልስ በቀለ እና ምንይሉ ወንድሙን የመሳሰሉ ተጫዋቾች እንደሚሳተፉ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ስልጠናው ረፋድ 4 ሰዓት ይጀመራል ተብሎ ቀድሞ የተነገረ ቢሆንም በአስገዳጅ ምክንያት የመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ወደ ከሰዓት 7:30 የተዘዋወረ ሲሆን የሚዲያ አካላትም በስፍራው እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል።