በውጤት ማጣት ውስጥ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች ዋና አሰልጣኛቸውን በማገድ ጊዜያዊ አሠልጣኝ መሾማቸው ታውቋል።
በ2016 የውድድር ዘመን አጋማሽ ወደ ቀደመው ክለባቸው ሲዳማ ቡና በመመለስ ክለቡ በሊጉ እንዲቆይ ማድረግ የቻሉት አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ዘንድሮ በመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ከክለቡ ጋር ለአንድ አመት ለመቆየት ቢስማሙም በቀጣይ በተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈት ማስተናገዳቸው ይታወሳል።
ይህንን የክለቡን አካሄድ የገመገመው የክለቡ ቦርድ በዛሬው እለት አዳማ በመገኘት አሰልጣኙን ማሰናበቱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች። የአሠልጣኝ ዘላለም ረዳት የነበሩት አሠልጣኝ አዲሴ ካሣ ደግሞ ቡድኑን በጊዜያዊነት እንዲያሰለጥኑ መመደቡ ታውቋል።