ተክለማርያም ሻንቆ ከክለቡ ጋር አይገኝም

ኢትዮጵያ መድን በግብ ጠባቂው ጉዳይ ደብዳቤ አውጥቷል።

ባለፈው የውድድር ዘመን አጋማሽ ኢትዮጵያ መድንን ተቀላቅሎ ክለቡን በማገልገል ላይ የነበረው ግብ ጠባቂው ተክለማርያም ሻንቆ ከክለቡ ጋር እንደማይገኝ ሶከር ኢትዮጵያ ተረድታለች ፤ ከሕዳር ወር መጀመርያ ጀምሮ ከክለቡ ጋር የማይገኘው ግብ ጠባቂው በአሁኑ ሰዓት በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኝ ሲሆን ክለቡ ስብስቡን እንዲቀላቀል ቀነ ገደብ አስቀምጦ ይፋዊ ደብዳቤ ያወጣ ሲሆን በቀጣይ ክለቡ የሚወስነው ውሳኔ ቢጠበቅም እስከ አሁን ግን ተክለማርያም ወደ ኢትዮጵያ እንዳልመጣ ለማወቅ ተችሏል።

ተክለማርያም ሻንቆ ከዚህ ቀደም በሀላባ ከተማ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ፣ ሀዋሳ ከተማ፣ በኢትዮጵያ ቡና፣ ሲዳማ ቡና ፣ መቻል፣ አዳማ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጫወቱ ይታወሳል ፤ የግብ ዘቡ ወደ አሜሪካ ያቀናበትን ምክንያት በዝርዝር ያሳወቀን ሲሆን በቀጣይ ይዘን የምንቀርብ ይሆናል።