አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት ቆይታቸው ዙርያ በዛሬው መግለጫ ምን አሉ?
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ያደረጋቸውን ጨዋታዎች እና የነበረውን ቆይታ አስመልክቶ የቡድኑ ጊዜያዊ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ዛሬ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የመሰብሰቢያ አዳራሽ በቦታው ለተገኙ የሚዲያ አካላት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
ከተነሳባቸው ጥያቄዎች መካከል በጊዜያዊነት ብሔራዊ ቡድኑ ለማሰልጠን የተረከቡበት ጊዜ ተገባዷል እና ስለ ቀጣይ ቆይታዎ ምን ሀሳብ አለዎት መቀጠል ያስባሉ ተብለው ሲጠየቁ አሰልጣኙም “ እንግዲህ ከመቀጠል ጋር በተገናኘ ያው የሚመለከተው አካል አለ ፤ ስራ አስፈፃሚው እኔ ለማገልገል ፍቃደኛ ነኝ ደስተኛም ነኝ” በማለት አጭር መልስ ሰጥተዋል።