የአሰልጣኞች አስተያየት | ፋሲል ከነማ 0-0 ሀዋሳ ከተማ

በርካታ ጥፋቶች በተፈፀሙበት እና ያለ ጎል ከተጠናቀቀው የፋሲል ከነማ እና ሀዋሳ ከተማ ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ ሁለቱ አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታን አድርገዋል።

አሰልጣኝ ወንድማገኝ ተሾመ – ሀዋሳ ከተማ (ጊዜያዊ)

“ጨዋታው ሁለት ዓይነት መልክ ነበረው የመጀመሪያው አርባ አምስት አንድ ልጅ ጎድሎብናል ያንን ለመቆጣጠር ብዙ ጥረት አድርገናል። በሁለተኛው አርባ አምስት የታክቲክ ለውጥ አደረግን ጨዋታውን በአቻ ለማጠናቀቅ ተገደናል።”

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ – ፋሲል ከነማ

“በጣም ፈታኝ ጨዋታ ነበር ፤ በሁለታችንም በኩል ለመሸናነፍ ከፍተኛ ጥረት እና ስሜት የበዛበት ጨዋታ ነበር የነበረው።”

ሙሉውን ለማድመጥ Link