የአሰልጣኞች አስተያየት | ቅዱስ ጊዮርጊስ 2-1 ኢትዮ ኤሌክትሪክ

የምሽቱ ጨዋታ በፈረሰኞቹ የበላይነት ከተቋጨ በኋላ ሁለቱ አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ ነበራቸው

አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

”ባለፉት ተከታታይ ጨዋታዎች ሶስት ነጥብ አለማግኘታችን ጫና ውስጥ ከቶናል ፣ ቅድሚያውን ወስደን ለመጫወት ነበር ያሰብነው ፤ ቀድመን ጎል ማግባት ችለናል። እንደ ጨዋታ ብዙ ማስተካከል የሚገቡን ጉዳዮች አሉ ብዬ አስባለሁ ፣ አሁንም በማጥቃቱ ብዙ መስራት አለብን ፤ ሁለት ጎል ማግባት ብቻ ሳይሆን ሌሎች የጎል እድሎችን መፍጠር አለብን።”

አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንጋታ – ኢትዮ ኤሌክትሪክ

”ጎል አግብተናል ማድረግ ያለብንን ነገር አድርገናል ፤ ያገኘነውን ኳሶች ብንጠቀም ጥሩ ነበር። ከትልቅ ቡድን ጋር ነው የተጫወትነው ጥሩ ተንቀሳቅሰናል። በመሸነፌ ቅር አይለኝም ከትልቅ ቡድን ጋር ነው የተጫወትኩት።”

ሙሉውን ለማድመጥ – Link