አዳማ ከተማ ወደ ሜዳው በተመለሰበት የሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታ ወልዋሎን 3ለ0 ከረታ በኋላ ሁለቱ አሰልጣኞች ለሶከር ኢትዮጵያ ጋር የድህረ – ጨዋታ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ አብዲ ቡሊ – አዳማ ከማ
“ጨዋታው ጥሩ ነበር ፣ ጨዋታውን በዕቅዳችን መሰረት ተቆጣጥረነዋል ፣ ሁለተኛው አርባ አምስት ላይ በተሻለ ግቦችን ሳንባክን አስቆጥረን ከተከታታይ ሽንፈቶች በመላቀቃችን ደስተኛ ነኝ።”
አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም – ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ
“የመጀመሪያው አጋማሽ 45ኛ ደቂቃ ላይ የገባብን ጎል ሁሉን ነገር ቀይሮታል ማለት ይቻላል እስከዛ ተመጣጣኝ የሆነ ጨዋታ ነበር።ቡድናችን በብዙ ነገር እየተጎዳ ስለሆነ ስነ-ልቦናውን መመለስ ነው ያቃተን።”
ሙሉውን ለማድመጥ – Link