ኢትዮጵያዊው አማካይ ጋቶች ፓኖም ወደ እስያ ማቅናቱ እርግጥ ሆኗል።
የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና፣ ወላይታ ድቻ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ መቐለ 70 እንደርታ፣ ፋሲል ከነማ እንዲሁም ከሀገር ውጭ ደግሞ በራሽያ እና ግብፅ ቆይታ የነበረው እና በዘንድሮ ዓመት ለኢትዮጵያ መድን ግልጋሎት እየሰጠ የሚገኘው ጋቶች ፓኖም ወደ እስያ ማቅናቱ ታውቋል።
ትናንት እኩለ ሌሊት ወደ መካከለኛው ምስራቋ ኢራቅ የተጓዘው ጋቶች ለየትኛው የኢራቅ ክለብ ለመፈረም ወይም የሙከራ ጊዜን ለማሳለፍ ተጓዘ የሚለውን ለማወቅ ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።ከኢራቅ ክለቦች ባለፈ የኢራን እና የሊቢያ ክለቦች በተመሳሳይ የተጫዋቹ ፈላጊዎች ስለመሆናቸው የተሰማ ሲሆን የእርሱ በቀጣይ በዚህ ዙርያ የሚኖሩ አዳዲስ መረጃዎችን እየተከታተልን የምናሳውቅ ይሆናል።