ምዓም አናብስት የመስመር ተከላካዩን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል

ባለፉት ስድስት ዓመታት በፈረሰኞቹ ቤት ቆይታ የነበረው ተጫዋች ወደ ምዓም አናብስት ለማቅናት ተቃርቧል።


መቐለ 70 እንደርታዎች ላለፉት ስድስት ዓመታት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የተሳኩ ዓመታት በማሳለፍ ባለፈው ክረምት ወደ ግብፁ ክለብ ሃራስ ኤል ሁዱድ ፈርሞ በአንዳንድ ምክንያቶች ከቡድኑ ጋር በስምምነት የተለያየው የመስመር ተከላካዩ ሄኖክ አዱኛ ለማስፈረም ተቃርበዋል።

በቅዱስ ጊዮርጊስ የስድስት ዓመት ቆይታው ሁለት የሊግ ዋንጫዎች ያነሳው ተከላካዩ ከዚህ ቀደም በጅማ አባጅፋር፣ ድሬዳዋ ከተማ፣ ሀላባ ከተማ እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን መጫወት የቻለ ሲሆን ስሙ ከደቡብ አፍሪካ እና የኢራቅ ክለቦችን ጨምሮ በሀገር ቤት ካሉ ክለቦች ጋሬ ሲያያዝ ቢቆይም ማረፍያው መቐለ 70 እንደርታ ለማድረግ ተቃርቧል።

ተጫዋቹ በዛሬው ዕለት መቐለ 70 እንደርታ ከወልዋሎ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ለመከታተል ወደ ስፍራው የሚያቀና ሲሆን በቅርቡ ዝውውሩን ይቋጫል ተብሎም ይጠበቃል።