የአሰልጣኞች አስተያየት | አዳማ ከተማ 1-2 ቅዱስ ጊዮርጊስ

ድራማዊ አጨራረስ በነበረው እና በፈረሰኞቹ የበላይነት ከተጠናቀቀው የምሽቱ ጨዋታ በኋላ የሁለቱ አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ በተለይ ለሶከር ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ አብዲ ቡሊ – አዳማ ከተማ

“ጨዋታው ሁለት መልክ የነበረው ነበር ፤ ነገርግን የጨዋታውን መንፈስ የሚቀይር ነገር ነው የተደረገው። በፕሪምየር ሊግ ደረጃ እንደዚህ አይነት ስህተቶች ይሰራሉ ብዬ አላስብም።”

አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ –  ቅዱስ ጊዮርጊስ

“በመጀመሪያ አጋማሽ እንደነበረን የበላይነት ቅድሚያ መውሰድ ነበረብን ፤ በሁለተኛው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች የማሸነፍ የተሻለ ጫና ፈጥረው ተጫውተዋል።ከልክ በላይ መጓጓቶች ሶስት አራት ዕድሎችን አለመጠቀማችን በኋላ ላይ ጫና ውስጥ ከቶናል።”

ሙሉውን ለማድመጥ – Link