የአሰልጣኞች አስተያየት | ስሑል ሽረ 1-2 መቻል

👉”በሁለተኛው አጋማሽ እንደነበረን እንቅስቃሴ ውጤቱ ጨዋታውን አይገልፀውም።” – ረዳት አሰልጣኝ ተገኝ ዕቁባይ

👉”ሜዳው በምንፈልገው ልክ እንድንቀሳቀስ አላስቻለንም ፤ በጣም አስቸጋሪ ነው።” – ረዳት አሰልጣኝ ደምሰው ፍቃዱ

 

መቻል ስሁል ሽረን ከረታበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች የአሰልጣኞች ቡድን አባላት ተከታዩን ሀሳብ ለሶከር ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።

ረዳት አሰልጣኝ ተገኝ ዕቁባይ – ስሁል ሽረ

“በመጀመሪያ አጋማሽ በማስቆጠር ረገድ ቅድሚያ ቢወሰድብንም በሁለተኛው አጋማሽ ወደ ጨዋታው ለመመለስ የተቻለንን ጥረት አድርገናል።ዛሬም ተደጋጋሚ ዕድሎችን ብንፈጥርም መጠቀም ሳንችል ቀርተናል።በሁለተኛው አጋማሽ እንደነበረን እንቅስቃሴ ውጤቱ ጨዋታውን አይገልፀውም።”

ረዳት አሰልጣኝ ደምሰው ፍቃዱ – መቻል

“ማሸነፋችን ጥሩ ነው ነገርግን ሜዳው በምንፈልገው ልክ እንድንቀሳቀስ አላስቻለንም ፤ በጣም አስቸጋሪ ነው።”

ሙሉውን ለማድመጥ – Link