የአሰልጣኞች አስተያየት | ሲዳማ ቡና 1-1 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

“ቡድኔ ወደምፈልገው መንገድ በጣም እየመጣ ነው።” አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ

“ሦስት ነጥብ አለማግኘታችን እንጅ የቡድናችን የማሸነፍ ሜንታሊቲ ጥሩ ነው።” አሰልጣኝ በጸሎት ልዑልሰገድ

ሲዳማ ቡና እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነጥብ ከተጋሩበት የምሽቱ ጨዋታ በኋላ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኝ ተከታዩን ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር አድርገዋል።

አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ – ሲዳማ ቡና

“ጨዋታው ጥሩ ነበር። ጎል ካስተናገድን በኋላ የተጫዋቾች መነሳሳት ጥሩ ነው። ቡድኔ ወደምፈልገው መንገድ በጣም እየመጣ ነው። ዛሬ ሙሉ ለሙሉ እናሸንፋለን ብዬ ነበር የመጣሁት ፤ ተጋጣሚያችን ዛሬ የነበረውን እንቅስቃሴ ከዚህ በፊት ዐላየሁበትም።”

አሰልጣኝ በጸሎት ልዑልሰገድ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

“በሁለታችንም ጥሩ ፉክክር የነበረበት ጨዋታ ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ ጥንቃቄ ከማብዛት የተነሳ ጎላችንን ለማስጠበቅ የነበረው ሂደት የማጥቃት እንቅስቃሴያችንን ቀንሶታል ብዬ አስባለሁ። ሦስት ነጥብ አለማግኘታችን እንጅ የቡድናችን የማሸነፍ ሜንታሊቲ ጥሩ ነው።”