ኢትዮጵያ መድን ወደ መሪዎቹ የተጠጋበትን ውጤት ካስመዘገበበት የምሽቱ ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ለሶከር ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ – ወላይታ ድቻ
“ጠንካራ ፉክክር የተደረገበት ጨዋታ ነበር ፤ ከሰው ሰራሽ ሜዳ ላይ እንደመምጣታችን ተጫዋቾቻችን በዚያ እሳቤ ውስጥ ናቸው።ከዚህ ለመውጣት የተወሰኑ ጨዋታዎችን በዚህ ሜዳ ማድረግ አለብን።”
አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ – ኢትዮጵያ መድን
“በአካላዊ መመዘኛዎች ጠንካራ ጨዋታ ነበር ፤ እንደ ወላይታ ድቻ ዓይነት በአከላዊ መመዘኛ ጠንካራ ቡድንን በዚህ ዓይነት ኳሶችን በሚያነጥር ሜዳ ስትገጥም እነሱን ተጠቃሚ ያደርጋል።ከመመራት ተነስተን ማሸናፍችን በራሱ ትልቅ ነገር ነው።”
ሙሉውን ለማድመጥ – Link