የአሰልጣኞች አስተያየት | ቅዱስ ጊዮርጊስ 1-0 ስሁል ሽረ

”ጨዋታውን ማሸነፋችን ተገቢ ነው” አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ

”ሜዳው ራሱ የሌቨሊንግ ክፍተት ስላለው ኳስ አውርደን በነፃነት መጫወት አልቻልንም ”ረዳት አሰልጣኝ በረከት ገብረመድህን

ፈረሰኞቹ ስሁል ሽረን በፍፁም ጥላሁን ብቸኛ ግብ በመርታት ተከታታይ ድል ካስመዘገቡበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገው ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

”ባለፉት ጨዋታዎችም ምንፈልገውን ነጥብ እንዳናገኝ ያደረገን ጎሎችን መሳታችን ነው ፣ እዛ ላይ በጣም ፎከስ አድርገን በጣም ሲሪየስ ሆነን መስራት እንደሚጠበቅብን ነው ያየውት። ወደመሪዎቹ መጠጋታችን ለአሰልጣኝ ቡድን አባላትም ለተጫዋቾችም ትልቅ የሞራል ስንቅ ይሆናል”

ረዳት አሰልጣኝ በረከት ገብረመድህን – ስሁል ሽረ

”በሁለተኛው አጋማሽ ንፋስ በጣም አውርደን ኳስ ለመያዝ አስቸግሮናል። በመጀመሪያ አጋማሽ ክፍተታችንን ሽፍነን አለመጫወታችን እነሱ የተሻለ እድል አግንተው አሸንፈው ሊወጡ ችለዋል። ስሁል ሽረ ኳስ አውርዶ ነው ሚጫወተው ፣ የሌቨሊንግ ክፍተት ስላለው ሜዳው እራሱ ኳስ አውርደን በነፃነት መጫወት አልቻልንም”

ሙሉውን ለማድመጥ LINK