የአሰልጣኞች አስተያየት | አርባምንጭ ከተማ 2-0 አዳማ ከተማ


👉 “የተጫወትንበት መንገድ ይበልጥ አስደስቶኛል” አሰልጣኝ በረከት ደሙ

👉 “ከተጠበቀው በታች ነው የተጫወትነው ”
አሰልጣኝ አብዲ ቡሊ

አርባምንጭ ከተማ ወደ ድል ከተመለሰበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ለሶከር ኢትዮጵያ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።


አሰልጣኝ አብዲ ቡሊ – አዳማ ከተማ

“የዛሬው ጨዋታ ከተጠበቀው በታች ነው የተጫወትነው። በመጀመርያው አርባአምስት የነበረን እንቅስቃሴ ደካማ ነው። አፈግፍገን ማጥቃት ላይ ተሳትፎ አልነበረንም። በጣም መሻሻል ይጠበቅብናል።”

አሰልጣኝ በረከት ደሙጰ- አርባምንጭ ከተማ

“ ጨዋታው አሪፍ ነበር። አዳማ ከተማ ባለሜዳ ስለነበረ ባለፈው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያደረገውን ጨዋታ በደንብ ተመልክተን ነበር። ደጋፊ ያላቸው ጥሩ ይንቀሳቀሳሉ እኛ ደግሞ ባለፈው አራፊ ስለነበርን በቂ የሚባል ዝግጅት አድርገን ነው የመጣነው በሁለቱም አጋማሾች በእንቅስቃሴ የጎል ዕድል በመፍጠርም የተሻልን ነበርን። ነጥቡ እጅግ በጣም ያስፈልገን ነበር። ነጥቡን ማግኘታችን አስደስቶኛል። ከእዛ እኩል ለኩል ግን የተጫወትንበት መንገድ ይበልጥ አስደስቶኛል።”

ሙሉን አስተያየት ለማድመጥ 👇