ኢትዮጵያ ቡና በናይጀርያዊው ዲቫይን ንዋቹኩ ብቸኛ ግብ ፋሲል ከነማን ከረታበት ጨዋታ በኋላ የሁለቱም ቡድን አሰልጣኞች የሰጡት አስተያየት።
አሰልጣኝ ነፃነት ክብሬ – ኢትዮጵያ ቡና
“በጨዋታው በተወሰነ መልኩ ከኳስ ውጭ የነበረን የመከላከል አደረጃጀት ጥሩ ነው ፤ በማጥቃቱ ብዙ ዕድሎች ያልፈጠርንበት ጨዋታ ነው።ትልቁ ነገር ልጆቹ መስጠት የሚችሉትን ዋጋ ከፍለዋል።”
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ – ፋሲል ከነማ
“ብዙ ከባድ ጨዋታ አልነበረም። ግን ቡድኑ ላይ በርካታ ተጫዋቾች የሉም ፤ በጉዳት ምክንያት ባለፉት ሁለት ሦስት ጨዋታዎች በርካታ ተጫዋቾች አጥተናል። የተወሰኑ ወጣት ተጫዋቾች ቀላቅለን ለመጫወት ሞክረናል። በተለይ ሁለተኛው አጋማሽ ብዙም መጥፎ አልነበርንም።”
ሙሉውን ለማድመጥ – Link