የአስራ አራተኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ በኢትዮጵያ መድን አሸናፊነት ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞቹ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
አሰልጣኝ ገብረመድን ሀይሌ – ኢትዮጵያ መድን
“ ጨዋታው ጥሩ ነው። የአሸናፊነት ስነ ልቦናችን በዚህ ደረጃ መቀጠሉ ትልቅ ነገር ነው። ተጫዋቾቼ ከጊዜ ወደ ጊዜ በራስ መተማመናቸው እየጨመረ አዕምሯቸው በዛው ልክ አድጓል።”
ጊዜያዊ አሰልጣኝ ወንድማገኝ ተሾመ – ሀዋሳ ከተማ
“ጨዋታው ጥሩ ነበር በመጀመርያው አጋማሽ አራት ለዜሮ ማለቅ ነበረበት ፤ ተደጋጋሚ ጎሎችን መሳታችን ዋጋ አስከፍሎን እንድንወጣ ተገደናል።”
ሙሉውን ለማድመጥ – LINK