የአሰልጣኞች አስተያየት | ወላይታ ድቻ 0-0 ሲዳማ ቡና

”ቢያንስ አንድ ነጥብ ይዘን መውጣት አለብን በሚል ገብተን ሶስት ለማግኘት ሞከርን ግን አልተሳካም” አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ

”ጨዋታው እንዳሰብነው አይደለም” አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ


ወላይታ ድቻ እና ሲዳማ ቡና ያደረጉት ጨዋታ ያለግብ ከመጠናቀቁ በኋላ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ – ወላይታ ድቻ

”ብዙ ግዜ አንድ የተለመደ ነገር አለ ድቻና ሲዳማ ሲጫወቱ፣ አለም ላይ እንደሚታየው አንድ ቲም አንድ ቲምን የማያሸንፈው ቲም አለ፣ ስለዚህ ያ መንፈስ ስላለ ትንሽ ዛሬ አንሸነፍም ቢያንስ አንድ ነጥብ ይዘን መውጣት አለብን በሚል ገብተን ሶስት ለማግኘት ሞከርን ግን አልተሳካም።”

አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ – ሲዳማ ቡና

”ጨዋታው እንዳሰብነው አይደለም፤ ምክንያቱም በመጀመሪያው አርባ አምስት ደቂቃ ሁለት ተጫዋቾ በጉዳት ወጥተውብናል። የፊት መስመሩን ሊፈፅምልህ የሚችል ተጫዋች ያስፈልጋል ፣የፊት መስመሩ ላይ ሰው ከሌለህ ያሉትም ተጨዋችች እየወጡ ከሆነ ያለህ አማራጭ የመጨረሻውን የመከላከል ኤሪያውን ጠንካራ ማድረግ ነው።”

ሙሉውን ለማድመጥ – Link