የአሰልጣኞች አስተያየት | ሀዋሳ ከተማ 1-1 ወልዋሎ ዓ/ዩ

👉 “ጨዋታው ጥሩ የሚባል ፉክክር ነበረው። ጊዜያዊ አሰልጣኝ ወንድማገኝ ተሾመ

👉 “ ተጭነን ለመጫወት አስበን ነበር ግን አልተሳካም።” ረዳት አሰልጣኝ አትክልቲ በርሄ

በወራጆች ዞን ውስጥ ያሉትን ቡኖች ያገናኘው ጨዋታ ያለ አሸናፊ ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞቹ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።


ረዳት አሰሰልጣኝ አትክልቲ በርሄ – ወልዋሎ ዓ/ዩ

“ ጨዋታውን የመጀመርያው አጋማሽ ጥሩ ነበርን። ሁለተኛው አጋማሽ ተጭነን መጫወት እያለብን ገና ከዕረፍት እንደገባን ጎል አገቡብን ተጭነን ለመጫወት አስበን ነበር ግን አልተሳካም።”

ጊዜያዊ አሰልጣኝ ወንድማገኝ ተሾመ – ሀዋሳ ከተማ

“ ጨዋታው ጥሩ የሚባል ፉክክር ነበረው። እንደጠበቅነው የመጀመርያው አርባ አምስት ሊሄዱልን አልቻሉም። አንድ ተጫዋች ጎሎብህ ተቋቁመህ አቻ መጨረስህ ጎል ማስቆጠር ደግሞ የቡድኑን ጥንካሬ ያሳያል። አሁንም ጎል አካባቢ እየተሳቱ ነው ያንን ለማረም እንሰራለን ብዬ አስባለው።”

ሙሉውን አስተያየት ለማዳመጥ 👇