የአሰልጣኞች አስተያየት | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1-1 ስሑል ሽረ

👉”ጨዋታውን በፈለግነው መንገድ አስኪደነዋል ብዬ አስባለሁ።” – አሰልጣኝ በጸሎት ልዑልሰገድ

👉”በሁለቱም አጋማሾች ከተጋጣሚያችን በተሻለ የግብ ዕድሎችን ብንፈጥርም መጠቀም ባለመቻላችን ዋጋ አስከፍሎናል።” – አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት

በአቻ ውጤት ከተጠናቀቀው ጨዋታ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ለሶከር ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ በጸሎት ልዑልሰገድ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

“ጨዋታውን በፈለግነው መንገድ አስኪደነዋል ብዬ አስባለሁ ፤ በኳስ ቁጥጥር ሆነ የግብ ዕድሎችን በመፍጠር የተሻልን ነበር በመጀመሪያው አጋማሽ ብቻ ሰባት ፣ ስምንት ዕድሎችን እንደመፍጠራችን አንዱን እንኳን ተጠቅመን ቢሆን ጨዋታውን መጨረስ እንችል ነበር።”

አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት – ስሑል ሽረ

“ጨዋታው ጠንካራ ነበረ ፤ በሁለቱም አጋማሾች ከተጋጣሚያችን በተሻለ የግብ ዕድሎችን ብንፈጥርም መጠቀም ባለመቻላችን ዋጋ አስከፍሎናል።”

ሙሉውን ለማድመጥ – LINK