የአሰልጣኞች አስተያየት | መቐለ 70 እንደርታ 2-0 አዳማ ከተማ

”በዚህ ሊግ ቀላል ነው የሚባል ጨዋታ የለም” አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ

”ሜዳው ኳስን ተቆጣጥሮ ለመጫወት ከባድ ሆኖብናል” አሰልጣኝ አብዲ ቡሊ

መቐለ 70 እንደርታ አዳማ ከተማን 2-0 በማሸነፍ ተከታታይ ድል ካስመዘገበበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ አሰልጣኞቹ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገው ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ – መቐለ 70 እንደርታ

”ጨዋታው ኖርማሊ በዚህ ሊግ ቀላል ነው የሚባል ጌም የለም ፤ በጣም ከባድ ነው እያንዳንዷን አይደለም ሦስት ነጥብ አንድ ነጥብ ለመውሰድም በጣም ከባድ ውጥረት ያለበት ነው። ማንም ያሸንፋል ብለህ ማትገምትበት ጨዋታዎች ነው ያሉት።”

አሰልጣኝ አብዲ ቡሊ – አዳማ ከተማ

”ጨዋታው ሲጀመር በመዘናጋት የተቆጠረብን ጎል ዋጋ አስከፍሎናል። መረጋጋት እና ራስን ወደአሸናፊነት ለመመለስ መሥራት እንዳለብን ነው የሚታየኝ። ሜዳው በአጠቃላይ ኳስን ተቆጣጥሮ ለመጫወት ከባድ ሆኖብናል፤ በዛ ላይ እኛ ከሽንፈት ለመውጣት የምናደርገው ጉጉት እና ችኮላ ዋጋ እያስከፈለን ነው።”

ሙሉውን አስተያየት ለማድመጥ LINK