”በማንኛውም ሰዓት ለማግባት ነው ጥረት ምናደርገው” አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይለ
”ጥድፊያዎች ችኮላዎች አሉ እሱን ማስተካከል አለብን” አሰልጣኝ ነፃነት ክብሬ
ኢትዮጵያ መድን በመጨረሻዎቹ ደቂቃ አቡበከር ሳኒ ባስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያ ቡናን ካሸነፉበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድን አስልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይለ – ኢትዮጵያ መድን
”በትዕግሥት ከቆየን ማግባት እንደምንችል ነግሬያቸው ነበር ይሄ ነው ሀፕንድ የሆነው። ኳስ ጨዋታ ትዕግሥት የሚፈልግ ነገር ነው። አሁን ባለቀ ደቂቃ ነው ያገባነው፤ በጣም ጥሩ ሰዓት ላይ ነው ያገባነው ከዛ በፊት አንድ ነገር ቢሆን አስቸጋሪ ነው ግን ደግሞ እኛ በማንኛውም ሰዓት ለማግባት ነው ጥረት ምናደርገው እንጂ በትዕግሥት ጠብቀን ለማግባት አይደለም ምናስበው።”
አሰልጣኝ ነፃነት ክብሬ – ኢትዮጵያ ቡና
” በስህተት በተቆጠረብን ጎል ልንሸነፍ ችለናል። ከኳስ ጋር የሚቀረን ነገር አለ ጥድፊያዎች ችኮላዎች አሉ እሱን ማስተካከል አለብን። በውጠቱ ደስተኛ አይደለሁም በርግጥ ግን አንዳንድ ግዜ መቀበል አለብህ።”
ሙሉውን አስተያየት ለማድመጥ LINK