ኢትዮጵያዊው አማካይ በኢራቅ ወሳኝ ግብ አስቆጥሯል።
በቅርቡ ኢትዮጵያ መድንን ለቆ የኢራቁን ኒውሮዝ የተቀላቀለው ጋቶች ፓኖም በክለቡ መለያ የመጀመርያ ግቡን አስቆጥሯል። ኒውሮዝ ከአል ሾርጦ ጋር ሁለት ለሁለት አቻ በተለያየበት የምሽቱ ጨዋታ ላይ ወሳኝዋ እና ቡድኑ ነጥብ ይዞ እንዲወጣ ያስቻለች የመጨረሻ ደቂቃ ግብ ያስቆጠረው አማካዩ ወደ ክለቡ ካቀናበት ጊዜ ጀምሮ በቋሚነት በማገልገል ላይ ይገኛል።
አስራ ስድስተኛው ሳምንት ላይ በደረሰው ሊግ ከመሪው አል ዛውራ በአስራ ሦስት ነጥቦች ዝቅ ብሎ በ14ኛ ደረጃነት የተቀመጠው ቡድኑ በሰንጠረዡ አጋማሽ ላይ ይገኛል።