በከፍተኛ ሊጉ ምድብ “ሀ” እየተሳተፈ የሚገኘው ደደቢት የቀድሞ ታሪካዊ ተጫዋቾችን ወደ አሰልጣኝ ቡድኑ አካትቷል።
በዘንድሮው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ለመወዳደር ፍቃድ አግኝቶ የተመለሰው ደደቢት በምድብ “ሀ” ተደልድሎ ካደረጋቸው 11 ጨዋታዎች 12 ነጥቦችን በመሰብሰብ 8ኛ ደረጃን ይዞ የመጀመሪያው ዙር መጠናቀቁ ይታወሳል።
ደደቢት በ2005 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቻምፒዮን ሲሆን በቡድኑ ውስጥ የነበሩ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባል የነበሩ ታሪካዊ ሦስት ተጫዋቾች አሁን ወደ አሰልጣኝነት መምጣታቸው ታውቋል።
በከፍተኛ ሊጉ የመጀመሪያ ዙር የክለቡ ተጫዋቾች የነበሩት ዳዊት ፍቃዱ እና ብርሃኑ ቦጋለ በረዳት አሰልጣኝነት እንዲሁም በዱራሜ በግብ ጠባቂነት ሲያገለግል የነበረው ግብ ጠባቂው ሲሣይ ባንጫ ግብ ጠባቂ አሰልጣኝ በመሆን መሾማቸው ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።