የአሰልጣኞች አስተያየት | መቻል 1-1 ባህር ዳር ከተማ

በጉጉት ከተጠበቀው እና በአቻ ውጤት ከተጠናቀቀው ጨዋታ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ለሶከር ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ – መቻል

“ጨዋታዎች በተከከታይ በማድረጋችን በሁለቱም ቡድኖች በኩል ድካም ይታያል ፤ እንኳን እኛም ማንቸስተር ሲቲም ተከታታይ ሰባት ጨዋታዎችን ተሸንፏል ስለዚህ ይህ በእግር ኳስ የሚያጋጥም ነገር ነው በሂደት ይስተካከላል።”

አሰልጣኝ ደግዓረግ ይግዛው – ባህር ዳር ከተማ

“በሁለቱም አጋማሾች ተጫዋቾቻችን ይዘነው የገባነው የጨዋታ ዕቅድ ለመተግበር የተቻላቸውን ጥረት አድርገዋል ፤ ጉዞው ረጅም ስለሆነ አሁንም መስራት ይጠበቅብናል።

ሙሉውን ለማድመጥ – Link