የአሰልጣኞች አስተያየት | ወልዋሎ ዓ.ዩ 1-0 ሀዲያ ሆሳዕና

“የዛሬው ውጤት ለቀጣይ ጨዋታዎች በጣም ያግዘናል።” ረዳት አሰልጣኝ አታኽልቲ በርሔ

“ዛሬ የተጫዋች አጠቃቀማችን በተወሰኑ መልኩ ፌል አድርጎብናል።” አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ

ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በቡልቻ ሹራ ብቸኛ ጎል ሀዲያ ሆሳዕናን 1ለ0 አሸንፎ በ14ኛ ጨዋታው ድል ካገኘ በኋላ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር አድርገዋል።



ረዳት አሰልጣኝ አታኽልቲ በርሔ – ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ

“እነሱ የሚገቡበትን ታክቲክ አውቀን ነበር። በድሉ በጣም ደስተኛ ነኝ። የሞት ሽረት አድርገን ሦስት ነጥብ ይዘን መውጣት አለብን ብለን አሳክተናል። የዛሬው ውጤት ለቀጣይ ጨዋታዎች በጣም ያግዘናል። የመጀመሪያ ድላችን ተስፋ ሳይቆርጡ ከጎናችን ለሆኑ ደጋፊዎች ማስታወሻ ይሁንልኝ።

አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ – ሀዲያ ሆሳዕና

“ጨዋታው ለእኛ ጥሩ አይደለም። ከመጀመሪያው ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ትክክል አልነበረም። በመልሶ ማጥቃት የነበረን ሚና በጣም አነስተኛ መሆኑ የጎል አጋጣሚ ለመፍጠር ምቹ አልሆነም። ዛሬ የተጫዋች አጠቃቀማችን በተወሰኑ መልኩ ፌል አድርጎብናል።”

ሙሉውን ለማድመጥ LINK