“አስበን የምንመጣውን ሜዳ ላይ እያገኘነው አይደለም።” አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ
“ጨዋታው በጠቅላላ ከምለው በላይ በጣም ጥሩ ነበር።” አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ
ኢትዮ ኤሌክትሪክ በናትናኤል ገብረጊዮርጊስ ሁለት ግቦች ሲዳማ ቡናን 2ለ0 ካሸነፈበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር አድርገዋል።
አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ – ሲዳማ ቡና
“ጨዋታው እንደጠበቅነው አይደለም ፤ አስበን የምንመጣውን ሜዳ ላይ እያገኘነው አይደለም ፤ ፊት መስመሩ ጉዳት በዝቶብናል አራት አምስት ከሜዳ የራቁ ተጫዋቾችን ነው እየተጠቀምን ያለነው። ስንሠራ እና ስናወራበት የነበረውን ሜዳ ላይ ብትንትን ብሎ ነው የምናገኘው።”
አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ – ኢትዮ ኤሌክትሪክ
“ጨዋታው በጠቅላላ ከምለው በላይ በጣም ጥሩ ነበር። ተጫዋቾቼ የተነጋገርነውን ነገር በትክክል ስለተገበሩት በጣም ደስ ብሎኛል። በተጫዋቾቼ ትልቅ ኩራት አለኝ።”
ሙሉውን ለማድመጥ LINK