ፕሪሚየር ሊግ፡ በ17ኛው ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲሸነፍ ፣ ቡና ፣ ድሬዳዋ እና ደደቢት ድል ቀንቷቸዋል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ሁሉም ጨዋታዎች ዛሬ ተደርገው ኢትዮጵያ ቡና ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ደደቢት ድል ቀንቷቸዋል፡፡ መሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲሸነፍ የሲዳማ ቡና እና ሀዲያ ሆሳዕና ጨዋታ በዝናብ ምክንያት ተቋርጧል፡፡

ወደ ድሬዳዋ ያቀናው ቅዱስ ጊዮርጊስ በድሬዳዋ ከተማ 1-0 ተሸንፏል፡፡ በ76ኛው ደቂቃ ከዮናስ ገረመው የተሸገረለትን ኳስ ተጠቅሞ ዳዊት እስጢፋኖስ የድሬዳዋን የድል ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡ ጥሩ እንቅስቃሴ በነበረበት ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊ የተሸለ እንቅስቃሴ ቢያደርግም ያገኛቸውን ጥቂት የግብ ማስቆጠር እድሎች መጠቀም አልቻሉም፡፡

አዲስ አበባ ስታድየም ላይ በደረጃ ሰንጠረዡ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ደደቢት እና አዳማ ከተማ ባደረጉት ጨዋታ ደደቢት 1-0 አሸንፎ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል፡፡ በመጀመርያው አጋማሽ ስዩም ተስፋዬ በፋሲካ አስፋው ላይ በሰራው ጥፋት በቀጥታ የቀይ ካርድ ከሜዳ መውጣቱን ተከትሎ ሁለተኛውን አጋማሽ በጎዶሎ ተጫዋች ለመጫወት የተገደደው ደደቢት በ46ኛው ደቂቃ ከጉዳት በተመለሰው ዳዊት ፍቃዱ አማካኝነት ባስቆጠረው ግብ ወሳን ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል፡፡ ለግቧ መቆጠር ጣጣውን ጨርሶ በማቀበል ከፍተናውን ሚና የተወጣው ሳሙኤል ሳኑሚ ነው፡፡

ጎንደር ላይ ዳሽን ቢራ ኢትዮጵየ ንግድ ባንክን አስተናገዶ ካለ ግብ አቻ ተለያቷል፡፡ ንግድ ባንኮች በ8ኛው ደቂቃ ያገኙትን የፍፁም ቅጣት ምት ሰለሞን ገብረመድህን ቢያስቆጠርም ኳሷ ከመመታቷ በፊት ሁለት የባንክ ተጫዋቾች መስመሩን አልፈው ገብተዋል በሚል በድጋሚ እንዲመታ ተደርጓል፡፡ ሁለተኛውን ምትም ደረጄ አለሙ መልሶታል፡፡ በፍፁም ቅጣት ምቱ ውሳኔ ከፍተና ውዝግብ የተከተለው ጨዋታ ግብ ሳቆጠርበት ተጠናቋል፡፡

PicsArt_1462300290976

ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከተማ ወላይታ ድቻን አስተናገዶ ካለ ግብ አቻ ተለያይቷል፡፡ ሀዋሳ ከተማዎች በኳስ ቁጥጥር የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረግ ቢችሉም ጠንካራውን የድቻ የተከላካ ክፍል ሰብረው ግብ ማስቆጠር አልቻሉም፡፡ በአንፃሩ ወላይታ ድቻዎች በጥልቀት በመከላከል በሚያገኟቸው አጋጣሚዎች የግብ እድል ለመፍጠር ሙከራ አድርገዋል፡፡ ከሀዋሳ በተሸለ ለግብ የቀረቡ ሙከራዎችም ማድረግ ችለዋል፡፡

አርባምንጭ ላይ አርባምንጭ በአቻ ጉዞው የቀጠለበትን ውጤት አስመዝግቧል፡፡ የአርባምንጭ ከተማ እና የመከላከያ ጨዋታ ጥቂት የግብ ሙከራዎች የተስተናገዱበት ሲሆን መከላከያዎች በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች የአቻ ውጤታቸውን አስጠብቀው ለመውጣት ጥረት ሲያደርጉ ተስተውለዋል፡፡ይህ የአቻ ውጤት ለአርባምንጭ ከተማ 4ኛ ተከታታይ አቻ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

PicsArt_1462300494509

አዲስ አበባ ስታድየም ላይ የእለቱ የመጨረሻ በሆነው ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ኤሌክትሪክን 1-0 በማሸነፍ በአሸናፊነቱ ቀጥሏል፡፡ ቀዝቃዛ እንቅስቃሴ እና ጥቂት የግብ ሙከራዎችን ባስተናገደው የመጀመርያ አጋማሽ ግብ ያልተስተናገደ ሲሆን በንፅጽር ከፍተና ፉክክር በታየበት የ2ኛው አጋማሽ በ58ኛው ኢትዮጵያ ቡና ያገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት  ጋቶች ፓኖም በአግባቡ ተጠቅሞ ቡናን ለድል አብቅቷል፡፡ የፍፁም ቅጣት ምቱ ውዝግብ ያስነሳ ሲሆን ከግቡ መቆጠር በኋላ የሃይል አጨዋወቶች ተበራክተው ታይተዋል፡፡ ውጤቱ ለቡና 4ኛ ተከታታይ ድል ፣ ለኤሌክትሪክ ደግሞ 4ኛ ተከታታይ ሽንፈት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ይርጋለም ላይ ሲዳማ ቡና ሀዲያ ሆሳዕናን አስተናገዶ ለ21 ደቂቃዎች ብቻ ተካሂዶ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ተቋርጧል፡፡ ነገ 04፡00 ላይ ከቆመበት እንዲቀጥልም ተወስኗል፡፡ ባለፈው ሳምንት ድሬዳዋ ላይ ድሬዳዋ ከተማ ከሲዳማ ቡና ጨዋታቸውን ሲያደርጉም በተመሳሳይ ከባድ ዝናብ ምክንያት መቋረጡ የሚታወስ ነው፡፡

 

የደረጃ ሰንጠረዥ

PicsArt_1462300439881

ከፍተኛ ግብ አግቢዎች

PicsArt_1462300371599

Leave a Reply