የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጥሪ አድርጓል

ለአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅት ለ29 ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ ለአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅት ለ29 ተጫዋቾች ጥሪ አደርገዋል። በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ማለትም ፡-

ግብ ጠባቂዎች

ታሪኳ በርገና (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ቤተልሔም ዮሐንስ (ሀዋሳ ከተማ)
ሮማን አንባዬ (ድሬዳዋ ከተማ)

ተከላካዮች

አሳቤ ሙሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ታሪካ ዴቢሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ትዕግሥት አዳነ (ሀዋሳ ከተማ)
ፀሐይነሽ ጁላ (ሀዋሳ ከተማ)
እፀገነት ብዙነህ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)
ብርቄ አማረ (መቻል)
ማሕደር ባየህ (አርባምንጭ ከተማ)
ፀጋ ንጉሤ (ሀዋሳ ከተማ)

አማካዮች

እመቤት አዲሱ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ሰናይት ቦጋለ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ፅዮን ፋየራ (መቻል)
ማዕድን ሳሕሉ (ሀዋሳ ከተማ)
ቤተልሔም መንተሎ (መቻል)
እፀገነት ግርማ (ሀዋሳ ከተማ)
መሳይ ተመስገን (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ብርቱካን ገ/ክርስቶስ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ዙፋን ደፈርሻ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)
ስመኝ ምህረት (አርባምንጭ ከተማ)

አጥቂዎች

ሎዛ አበራ (ዲሲ ፓወር /ዩኤስኤ)
ሴናፍ ዋቁማ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
አረጋሽ ካልሳ (ያንግ አፍሪካንስ / ታንዛንያ)
እሙሽ ዳንኤል (ሀዋሳ ከተማ)
አሪያት ኦዶንጎ (ያንግ አፍሪካንስ / ታንዛንያ)
ምርታት ፈለቀ (አርባምንጭ ከተማ)
ንግሥት በቀለ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ማሕሌት ምትኩ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)

ከነገ (እሁድ ጥር 25) ከ8፡00 ጀምሮ አዲሱ ገበያ አካባቢ የሚገኘው “ጋራ ላይ ሆቴል” ሪፖርት አድርገው በመሰባሰብ ዝግጅት እንዲጀምሩ ጥሪ ቀርቧል።