ኢንተርናሽናል ዳኛው በአዳማ አይገኙም

ከትናንት በስቲያ በተካሄደው በሸገር ደርቢ ጨዋታ ከዳኝነት ጋር ተያይዞ በተፈጠረው ቅሬታ ዙርያ ብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ውሳኔ አሳልፏል።

በ18ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በመጀመሪያ የጨዋታ ዕለት ባሳለፍነው እሁድ 9 ሰዓት ላይ በሸገር ደርቢ ኢትዮጵያ ቡና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር አቻ በተለያዩበት ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊሶች በጨዋታው ዋና ዳኛ ቴዎድሮስ ምትኩ ላይ የነበራቸውን ቅሬታ ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ማሳወቃቸውን ዘግበን ነበር።

ሶከር ኢትዮጵያ አሁን እንዳገኘችው መረጃ ከሆን ዋና ዳኛ ቴዎድሮስ ምትኩ በአሁኑ ሰዓት ከአዳማ ሆቴላቸው በመውጣት ወደ አዲስ አበባ ማቅናታቸው ሲሰማ በምትካቸው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማም ስለመተካታቸውም እንዲሁ አውቀናል።

ዋና ዳኛ ቴዎድሮስ ምትኩ ከሆቴል መውጣታቸው ከባለፈው ጨዋታ ጋር በተፈጠረ ግድፈት እንደሆነ ለማጣራት ያደረግነው ጥረት ባይሳካም በምትካቸው ሌላ ዳኛ እንዲመጣ መደረጉ ውሳኔ ተወስኖባቸው ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።

ከዚህ ቀደም እንዲህ ያለ መሰል ስህተት በሰሩ ዳኞች ላይ ብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ የተለያዩ ውሳኔዎች መወሰኑ ይታወቃል።