ከቀናት በፊት ከሻምፕዮኖቹ ጋር በስምምነት የተለያየው አጥቂው ወደ ሌላው የሊጉ ክለብ ለመቀላቀል ተስማምቷል።
አንድ ዓመት ተኩል አብሮት ከቆየበት እና የሊጉን ዋንጫ ከፍ ካደረገበት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የነበረው ቆይታ ከክለቡ ጋር በስምምነት የተለያየው አጥቂው ቢንያም ጌታቸው ወደ ሌላኛው የሊጉ ክለብ ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል።
ቢንያምን የግሉ ለማድረግ የተቃረቡት ፋሲል ከነማዎች ሲሆኑ በአጠረ ጊዜ ውስጥ ዝውወረሩን እንደሚቋጩ ይጠበቃል።
በውድድር ዓመቱ ብዙም የመጫወት ዕድል ያልነበረው ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም በሀምበሪቾ፣ አዲስ አበባ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ መጫወቱ ይታወሳል።
በተከታታይ ጨዋታ ድል ማድረጋቸውን ተከትሎ ደረጃቸውን እያሻሻሉ የሚገኙት ዐፄዎቹ የአጥቂውን ዝውውር ካገባደዱ በኋላ ተጨማሪ ተጫዋቾች ያስፈርማሉ ተብሎም ይጠበቃል።