ከደቂቃዎች በፊት ባደረስናችሁ መረጃ መሰረት ሦስተኛው ዙር የኢትዮጵያ ዋንጫ በየት ከተማ እንደሚካሄድ ታውቋል።
ከየካቲት 5-7 ባሉት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ሊካሄድ አስቀድሞ መርሐግብር የወጣለት የኢትዮጵያ ዋንጫ ሦስተኛ ዙር ጨዋታዎች በመዲናዋ በሚካሄደው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ምክንያት በአዲስ አበባ እንደማይካሄድ ገልጸን አወዳዳሪው አካል ውድድሩ በወጣለት ፕሮግራም መሠረት በሌላ ስታዲየም እንዲካሄድ ጥረት እያደረገ ሲሆን ምን አልባት ሰበታ ከተማ ላይ ለማድረግ መታሰቡን ጠቁመን ነበር።
ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባገኘችው መረጃ መሠረት ጨዋታዎቹ በሰበታ ከተማ ለማድረግ መወሰኑን እና ለክለቦች ደብዳቤ መላኩን አረጋግጠናል።