ከነዓን ማርክነህ አዲስ ክለብ አግኝቷል

ኢትዮጵያዊው ተጫዋች ወደ ሌላኛው የሊቢያ ክለብ አቅንቷል።

በክረምቱ የዝውውር መስኮት መቻልን በመልቀቅ ወደ ሊቢያው አል መዲና አቅንቶ ላለፉት ወራት ከክለቡ ጋር ቆይታ በማድረግ በስምንት ጨዋታዎች ሦስት ግቦች በማስቆጠር መልካም አጀማመር ያደረገው አማካዩ ባልታወቀ ምክንያት ከትሪፖሊው ክለብ ተለያይቶ ወደ ሌላው የሊቢያ ክለብ ሸባብ አል ጋሀር ተቀላቅሏል። ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ በአዳማ ከተማ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና መቻል እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መጫወት የቻለው አማካይ ከአዲሱ ክለቡ ጋር ልምምድ መሥራት የጀመረ ሲሆን ክለቡ በነገው ዕለት ከአል ባሻየር ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ይሳተፋል ተብሎ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያዊውን አማካይ ያስፈረመው ክለብ በሊቢያ ፕሪሚየር ሊግ ምድብ ሦስት ላይ የሚሳተፍ ክለብ ሲሆን ከኦሎምፒክ አዛውያ እና ስዌህሊ የተባሉ ክለቦች በመቀጠል በ3ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ክለብ ነው።