ከፍተኛ ሊግ  | ዱራሜ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ቀጥሯል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊጉ የምድብ “ሀ” ተካፋዩ ክለብ አዲስ አሰልጣኝ ሾሟል።

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ “ሀ” ተወዳዳሪ የሆነው ዱራሜ ከተማ የመጀመሪያውን ዙር የሊግ ውድድሩን በስምንት ነጥቦች ዘጠነኛ ደረጃ ላይ የቋጩ ሲሆን አሰልጣኝ አዲሱ ዶይሶን ለደደቢት አሳልፎ መስጠቱን ተከትሎ የአዲስ አሰልጣኝ ሹመትን ክለቡ አድርጓል።

የቡድኑ አሰልጣኝ በመሆን የተሾመው ብሩክ ሲሳይ ነው ፥ ከዚህ ቀደም በሀምበሪቾ የተጫዋችነት ዘመኑን ያሳለፈው እና በመቀጠልም በሀምበሪቾ ከከፍተኛ ሊጉ አንስቶ እስከ ፕሪምየር ሊጉ ድረስ በረዳት አሰልኝነት እና በዋና አሰልጣኝነት ለአራት ተከታታይ ዓመት በመስራት ግልጋሎት የሰጠ ሲሆን አሁን ደግሞ የከፍተኛ ሊጉን ክለብ ለማሰልጠን ተረክቧል።

ቡድኑም በዛሬው ዕለት የምድቡን መሪ ሸገር ከተማን በማስተናገድ ዙሩን ይጀምራል።