አሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረቡ

አሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከካሜሩን ጋር ለሚያደርገው የ2ኛ ዙር ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ዓለም ዋንጫ የማጣርያ ጨዋታ ዝግጅት ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል።

ዚምባብዌ ራሷን በማግለሏ ምክንያት ወደ ተከታዩ ዙር በፎርፌ ያለፈው ቡድኑ በሁለተኛው ዙር በየካቲት ወር መጨረሻ እና መጋቢት መጀመርያ ከካሜሩን ጋር የደርሶ መልስ ጨዋታዎች የሚያደርግ ሲሆን ከየካቲት 13 ጀምሮ ዝግጅት እንደሚጀምሩም ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች

ስመኝሽ ፍቃዱ (አዲስ አበባ ከተማ)
ሸዊት አብርሀ (ሲዳማ ቡና)
ቆንጂት አበራ (ጉለሌ ክ/ከተማ)

ተከላካዮች

ሰርካለም ሻፊ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ካምላክነሽ ሀንቆ (ሀዋሳ ከተማ)
ዝናሽ ሰለሞን (ሀምበርቾ)
ፍቅርአዲስ ገዛኸኝ (ቦሌ ክ/ከተማ)
ለምለም አስታጥቄ (ሀዋሳ ከተማ)
መቅደስ ከበደ (ሲዳማ ቡና)
ቤተልሔም መስፍን (አዲስ አበባ ከተማ)

አማካዮች

ብርሀን ኃይለሥላሴ (ኤሌክትሪክ)
ሄለን መንግሥቱ (ቂርቆስ ክ/ከተማ)
ስመኝ ታደሰ (ንፋስ ስልክ)
ብዙዓየሁ ፀጋዬ (ቦሌ ክ/ከተማ)
ቅድስት ገነነ (ባህር ዳር ከተማ)
ሚሌን ጋይም (ቦሌ ክ/ከተማ)
ሜላት ጌታቸው (ቦሌ ክ/ከተማ)

አጥቂዎች

ህዳአት ካሡ (ኤሌክትሪክ)
ሊዲያ ኢያሱ (ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ)
አሰገደች ሸጎ (ቂርቆስ ክ/ከተማ)
ታሪክ ጴጥሮስ (ሀዋሳ ከተማ)
ምትኬ ብርሀኑ (ሲዳማ ቡና)
ሰላማዊት መንገሻ (ባህር ዳር ከተማ)