ፋሲል ገብረሚካኤል እና ስሑል ሽረ ተለያይተዋል

በክረምቱ የዝውውር መስኮት ስሑል ሽረን ተቀላቅሎ የነበረው ግብ ጠባቂ ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይቷል።

በክረምቱ የዝውውር መስኮት ስሑል ሽረን ተቀላቅሎ ላለፉት ወራት ከክለቡ ጋር ቆይታ ያደረገው ግብ ጠባቂው ፋሲል ገብረሚካኤል ከቀናት በፊት ያስገባው የመልቀቅያ ደብዳቤ ተቀባይነት ማግኘቱን ተከትሎ ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይቷል።

በዳሽን ቢራ ተስፋ ቡድን የግብ ጠባቂነት ህይወቱን የጀመረው ተጫዋቹ በማስከተልም በደደቢት፣ ሰበታ ከተማ፣ ባህርዳር ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም ከ17 ዓመት በታች እና ዋናው  ብሔራዊ ቡድን መጫወቱ ሲታወስ በግማሽ የውድድር ዓመት የሽረ ቆይታውም በአራት ጨዋታዎች ተሰልፎ በድምሩ 360 ደቂቃዎች ቡድኑን ማገልገል ችሏል።