የጦና ንቦቹ ከአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ጋር በጋራ ስምምነት መለያየታቸው ታውቋል።
ወደ ቀድሞው ክለቡ በመመለስ ላለፉት አንድ ዓመት ተኩል ያህል ጊዜያት በወላይታ ድቻ ቆይታን ያደረገው የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች የሆነው ባዬ ገዛኸኝ በክለቡ እና በተጫዋቹ መካከል በተደረገ የጋራ ስምምነት ቀሪ የውል ዘመን እየቀረው መለያየቱ ታውቋል።
ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጋር በወላይታ ድቻ መለያ መታወቅ የቻለው አጥቂው በመቻል ፣ ሲዳማ ቡና ፣ ባህር ዳር ከተማ ፣ ሀዲያ ሆሳዕና ተጫውቶ ካሳለፈ በኋላ ወደ ቀደመ ክለቡ ወላይታ ድቻ በመመለስ በአምበልነት ጭምር ቡድኑን ሲያገለግል መቆየቱም ይታወሳል።