ትውልደ ኢትዮጵያዊው ወደ ቀድሞ ክለቡ ተመለሰ

ሀሩን ኢብራሂም ከኖርዌዩ ታላቅ ክለብ ሞልደ ጋር ተለያይቷል።

ከሁለት ዓመት በፊት ሞልደ ባደረገው የቻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣርያ ጨዋታ ተሳታፊ የነበረው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሀሩን ኢብራሂም የኖርዌዩን ክለብ በመልቀቅ ባለፈው የውድድር ዓመት በውሰት ለተጫወተበት የስዊድኑ ‘GAIS’ በቋሚነት ፈርሟል። በ2021 GAIS’ን ለቆ ወደ Molde በማቅናት በክለቡ የአንድ ዓመት ቆይታ አድርጎ ለተሻለ የጨዋታ ጊዜ  በ Sirius ባለፈው የውድድር ዓመት ደግሞ በ Gais የውሰት ቆይታዎች የነበረው ይህ በግራ ተከላካይነት እና በአማካይነት መጫወት የሚችለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ በስዊድኑ GAIS ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ለመቆየት ተፈራርሟል።

ከፊርማ ስነ ስርዓቱ በኋላ ተጫዋቹ በክለቡ ለመቆየት መወሰኑ ደስተኛ እንደሆነ በመግለፅ በቆይታው እንደ ባለፈው ዓመት ጠንክሮ እንደሚሰራ ሲገልፅ የክለቡ ቴክኒካል ዳይሬክተር Magnus Sköldmark በበኩላቸው “ከሞልደ ጋር ጥሩ ውይይት አድርገን በስተመጨረሻ ስምምነት ላይ ደርሰናል ሀሩን አሁን በቋሚነት የGAIS አካል ነው፤ እስከ 2029 የሚቆይ ኮንትራት ፈርመናል በዚህም ደስተኞች ነን” ብለዋል።