የአአ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለ8ኛ ጊዜ ያዘጋጀው ሲቲ ካፕ የፊታችን ጥር 4 ይጀመራል፡፡
*በውድድሩ 7 የአአ ክለቦች እና ሙገር ሲሚንቶ በተጋባዥነት ይሳተፋሉ፡፡
*በብሄራዊ ቡድኑ ዝግጅት ምክንያት ለ40 ቀናት የተቋረጠው ፕሪምየር ሊግ አለመኖርን ተከትሎ ውድድሩ መዘጋጀቱ ቡድኖቹ በውድድር መንፈስ ውስጥ እንዲቆዩ ያግዛል ተብሏል፡፡
የእጣ አወጣጡ ስነስርአት ቅዳሜ ተካሂዶ በምድብ 1 ደደቢት፣ መከላከያ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በምድብ 2፡ ቅ/ጊዮርጊስ ፣ ኢትዮጵያ መድን፣ ፣ ሙገር ሲሚንቶ እና መብራት ኃይል ተደልድለዋል፡፡
ጥር 4 በሚደረገው የመክፈቻ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ከ ደደቢት ይጫወታሉ
ውድድሩ ከዚህ ቀደም 7 ጊዜ ሲካሄድ ቅዱስ ጊዮርጊስ 3 ጊዜ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና መብራት ኃይል 2 ጊዜ ዋንጫውን አንስተዋል፡፡ አምና በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያ ቡና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አሸንፎ የዋንጫ ባለቤት መሆኑ ይታወሳል፡፡
© ሶከር ኢትዮጵያ